የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የዩኔስኮ የቴክኒክና ሙያ ማዕከል አባል ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የዩኔስኮ የቴክኒክና ሙያ ማዕከል አባል ሆነ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2017(ኢዜአ)፦ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት የቴክኒክና ሙያ ማዕከል(UNEVOC) አባል መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዩኔስኮ ኢንስቲትዩትን አባል አድርጎ መቀበሉን ማስታወቁንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።
ማዕከሉ አባል ሀገራት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ድጋፍ ያደርጋል።
በተጨማሪም የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች መፍጠር፣ የፈጠራ ፕሮጀክቶች መደገፍ፣ የዓለም አቀፍ የእውቀትና ክህሎት ሽግግር እንዲሁም ትስስር እንዲፈጥሩ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።