ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የሰላም ስምምነትን ፈፅመው በምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን - ሰኚ ነጋሳ - ኢዜአ አማርኛ
ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የሰላም ስምምነትን ፈፅመው በምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን - ሰኚ ነጋሳ
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 13/2017(ኢዜአ)፦ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ሰኚ ነጋሳ ገለጸ።
የበኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት በምክክሩ እየተሳተፉ ሲሆን የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በቅርቡ ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረመው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ሰኚ ነጋሳ የምክክሩን አስፈላጊነት አፅኦት ሰጥቶ፣ የኦሮሞ ህዝብም ምክክሩ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል፡፡
ምክክሩ ምሉዕ የሚሆነው ሁሉም ዜጋ ሲሳተፍበት መሆኑን የተናገረው አመራሩ ለዚህም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ እንደነሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በዚህ የምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡
በምክክር መድረኩ ሃሳቦችን በነፃነት አንስተን፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከራክረን፣ ለዜጎች ሰላምና ደህንነት የሚጠቅሙ ሀሳቦችን ይዘን ስንወጣ ነው ምክክሩ የተሳካ የሚሆነው ያለው ሰኚ ነጋሳ ለዚህም ሁላችንም ለምክክሩ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መድረኩን በማመቻቸቱ ምስጋና ማቅረባቡን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡