ቀጥታ፡

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጠ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 13/2017(ኢዜአ)፦ በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጧል።


 

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ በመመረጡም የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ በዓለም መድረክ ውጤታማ ሆና ከፍ እንድትል እና ወደ ቀድሞ ዝናና ውጤታማነት ለመመለስ እንዲሰራ እንዲሁም መጪው የስራ ጊዜው ውጤታማ እና ስኬታማ እንዲሆን ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም