የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 12/2017(ኢዜአ)፦ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ አበባ ገቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክታቸው ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ።

በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም