ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለ ስምንት ወለል የመኪና ማቆሚያ ሕንጻ አስመረቀ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 12/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ22 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለበረራ ባለሞያዎች ያስገነባውን ባለ 8 ወለል ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ሕንጻ ዛሬ አስመርቋል።

በ48 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው እጅግ ዘመናዊ ህንፃ በአንድ አመት ከአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን ከ 1 ሺህ 300 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል መሆኑም ታውቋል።


 

ሕንጻው ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ፣ በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ የተገጠመለት፣ እንዲሁም ድንገተኛ የእሳት አደጋን መቋቋም እንዲያስችል ተደርጎ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ የተገነባ መሆኑም ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት በ2ኛ ዙር የቤት ግንባታ ፕሮግራም ለ5 ሺህ ሰራተኞቹ የመኖሪያ ቤት ግንባታ እያከናወነ መሆኑንም የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም