ኢትዮጵያን በምክክር ለመገንባት ያለመ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያን በምክክር ለመገንባት ያለመ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው
አዳማ ፤ታሥሳስ12/2017 (ኢዜአ)፡- "ተመካክረን ኢትዮጵያን እንገንባ፤ እኔም ለሀገሬ እመክራለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የቀድሞ ኦነግ አመራር አባል አቶ ሌንጮ ባቲ እና አቶ ኢብሳ ነገዎን ጨምሮ ሌሎችም ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በመድረኩ ተገኝተዋል።
ቀደም ሲል በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ላይ ከሰባት ሺህ በላይ የህዝብ ተወካዮች የተሳተፉበት የምክክር መድረክ መካሄዱን የሚታወስ ነው።