የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
ድሬዳዋ፤ ታህሳስ 12/2017(ኢዜአ)፦ " ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነትና ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ አገር አቀፍ የሰላም ጉባዔ እና የምስጋና መርሐ ግብር በድሬደዋ እየተካሄደ ነው።
በኮንፈረንሱ ላይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂዎች፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሐመድ ኢድሪስ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ ወይዘሮ ፈትህያ አደን፣ የድሬደዋ ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች እና ዑጋዞችን ታድመዋል።
የድሬደዋ አስተዳደር የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሐፊ ፓስተር ሚልኪያስ ታዬ፤ ጉባኤው ሰላም በአገሪቱ በዘላቂነት አፅንቶ ለማስቀጠል የሃይማኖት አባቶችና ምዕምናን ይበልጥ እንዲሰሩ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰላም ጉባኤውና የምስጋና መርሐ ግብሩን የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ ከድሬደዋ አስተዳደር እና ከአስተዳደሩ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው መሆኑ ተመልክቷል።