የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ወደ ሊቢያ አቀና - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ወደ ሊቢያ አቀና
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) ከሱዳን ጋር ለሚያደርጋቸው የማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ወደ ሊቢያ አምርቷል።
ስምንተኛው የቻን ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በኬንያ፣ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።
በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ የመጨረሻ ዙር ማጣሪያዋን ከሱዳን ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታዋን ታህሳስ 13 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም በሊቢያ ቤንጋዚ ታደርጋለች።
የዋልያዎቹ ስብስብ ጨዋታዎቹን ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን ወደ ሊቢያ ማምራቱን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በጊዜያዊ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለጨዋታዎች ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጎ ቡድኑ ከታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ ልምምዱን በአዲስ አበባ ሲያደርግ ቆይቷል።
የአገር ውስጥ የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አድርጓል።
ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች ለውድድሩ ማለፏን ታረጋግጣለች።
የአፍሪካ አገራት ዋንጫ (ቻን) የአገር ውስጥ ሊግ ተጫዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት ውድድር ነው