ቀጥታ፡

ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ትኩረት መስራት አለባቸው- ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2017 (ኢዜአ)፦ ዲፕሎማቶች የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ትኩረት እንዲሰሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) አሳሰቡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በናይሮቢ ኤምባሲ በመገኘት ከኤምባሲው ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ ዲፕሎማቶች የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ ትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ በሚኒስትሩ ለመራው ልዑክ በኤምባሲው አቀባበል ማድረጋቸውንም በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኬንያ ባለስልጣናት ጋር የአገራቱን የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ዛሬ በናይሮቢ ውይይት ማድረጉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም