የፕሪሚየር ሊጉ ቀጣይ መርሃ ግብሮች በአዳማ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ ቀጣይ መርሃ ግብሮች በአዳማ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11/2017(ኢዜአ)፦ የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ12ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት የሚከናወኑ ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።
ሊጉ ከ1ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት የነበሩ የጨዋታ መርሃ ግብሮች በድሬዳዋ ስታዲየም መከናወናቸው ይታወቃል።
ከ12ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ያሉ የጨዋታ መርሃ ግብሮች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚከናወን ማህበሩ አመልክቷል።
ውድድሩ ከታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ አክሲዮን ማህበሩ አስታውቋል።