የኃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም ባላቸው ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም ባላቸው ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው
ድሬዳዋ፤ታህሳስ 11/2017(ኢዜአ)፦የኃይማኖት ተቋማት ለዘላቂ ሰላም ባላቸው ሚና ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው።
ፓናሉ፥ ኃይማኖቶች ለሰላም፣ለአንድነት፣ለአብሮነትና ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።
ውይይቱ የኃይማኖት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እያከናወኑት ያለውን ተግባር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
በፓናል ውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ኡጋዞችና አባ ገዳዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የካቢኔ አባላት የውይይቱ ተካፋዮች ናቸው።
ውይይቱ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከድሬዳዋ አስተዳደር ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።