የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግን ተቀብለው አነጋግረዋል።
የስራ ኅላፊዎቹ በሁለትዮሽ፣ በአህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የጋራ ጥቅሞች ዙሪያ መክረዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት የኢትዮ-ቻይና በሁኔታዎች ወደማይለዋወጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማደጉን አስታውሰው፤ አሁንም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው ጥረት የቻይናን ያልተቆጠበ ድጋፍ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂም ከቻይና አፍሪካ ትብብር ማዕቀፍ ዓላማዎች ጋር የተጣጣም ስለመሆኑ አስረድተዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች የቻይና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግ በበኩላቸው የኢትዮ- ቻይና ትብብርና አጋርነት ደረጃ ማድጉን አንስተዋል።
የሁለቱን ሀገራት አጋርነት ቀጣይነት ባለው መልኩ ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።