ቀጥታ፡

በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በካንቤራ ከተማ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10/2017(ኢዜአ)፦ በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በአውስትራሊያ ካንቤራ ከተማ ጉብኝት አድርጓል።

ሚኒስትሯ ከአውስትራሊያ በካንቤራ ከተማ የፌደራል መንግስት አስተዳደር የተለያዩ የስራ ዘርፍ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ጉብኝቱ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ አረንጓዴ ልማት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና የተለያዩ ዘርፎች ልምድ ለመለዋወጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ልዑኩ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ጥምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ የተሰራው የቤት ልማትን እና የአውስትራሊያ የጦር መታሰቢያ ሙዚየን ጎብኝቷል።


 

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያና አውስትራሊያ በኮሪያ ጦርነት ወቅት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር ባደረጉት ተሳትፎ መስዋዕትነት ለከፈሉ ወታደሮች የመታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸውን በካንቤራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም