ሕዝብና መንግስት ለዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ ከተንቀሳቀሱ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና ነቀምት ከተማ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው - ተስፋዬ በልጂጌ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 08 /2017(ኢዜአ)፦ ሕዝብና መንግስት ለዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ ከተንቀሳቀሱ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና ነቀምት ከተማ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) ገለፁ።

ሚኒስትሩ በወለጋ እና በአካባቢው የመስክ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በምልከታቸውም በአካባቢው ተስፋ ሰጭ የሰላም እንቅስቃሴዎች መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በወለጋና አካባቢው ይታዩ የነበሩት ተደጋጋሚ ግጭትና ውድመቶች እንዲሁም የሰላም ችግሮች በህዝቡ ባለቤትነትና ተሳትፎ ፣ በአመራሩ ቁርጠኝነትና አስተባባሪነት፣ በፀጥታ ኃይሉ መስዋዕትነት ተስፋ ሰጪ የሰላም እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሀሆኑን ገልፀዋል።

አሁን ላይ አካባቢዎቹ በእጅጉ ወደተሻለ የሰላም ግንባታ እና የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ህዝብና መንግስት በጋራ ለዘላቂ ሰላምና ልማት ከተንቀሳቀሱ ለውጥ መምጣት እንደሚችል በምስራቅ ወለጋ ዞን እና ነቀምት ከተማ በነበረኝ በመስክ ምልከታ አረጋግጫለሁም ብለዋል፡፡

በከፍተኛ መስዋዕትነት የተገኘውን ሰላም መጠበቅ እና ማስቀጠል ከሁሉም አካላት መጠበቅ እንደሚገባም መግለፃቸውንም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም