ሚኒስትሩ የ2017 አዲስ ገና የንግድ ባዛር እና ኤግዚቢሽንን በይፋ ከፈቱ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2017(ኢዜአ)፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሣሁን ጎፌ(ዶ/ር) የ2017 አዲስ ገና የንግድ ባዛር እና ኤግዚቢሽንን በይፋ ከፈቱ።

ሚኒስትሩ በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ ሀገራችን ባለፉት አምስት ወራት ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው ማግኘት የሚገባትን ትሩፋቶች መቋደሷን ገልጸዋል።

ባለፉት አምስት ወራት ከወጪ ንግድ ሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤት መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

የሀገር ውስጥ ገበያውን ለማረጋጋት በተሰራው ስራ ሕግና ስርዓት አክብረው ለመስራት ፍቃደኛ ባልሆኑ ከመቶ ስምንት ሺህ በላይ ነጋዴዎች ሕጋዊ እርምጃ እንደተወሰደበት ገልጸዋል።

አዲስ ገና ባዛርና ኤግዚቢሽን ከታህሳስ 08 ቀን 2017 አስከ ታህሳስ 28/ 2017 ዓም ድረስ ክፍት እንደሚደረግ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም