የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ሊያካሂድ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ሊያካሂድ ነው
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስምምነቱን ለማጽናትና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ አካላት የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑንም ገልጿል።
በተጨማሪም መላው የአገሪቱ ሕዝብ ለሰላም ያለውን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይበት፣ አብሮነቱን የሚያጠናክርበትና ለሰላም ግንባታ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የሚያጎላበትን መድረክ ለማመቻቸት እየሰራ ስለመሆኑም ገልጿል።
በዚህም ጉባዔው ''ኃይማኖት ለሰላም ለአንድነትና ለመከባበር'' በሚል መሪ ሃሳብ አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል።
ኮንፍረንሱ በሁሉም ክልል ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ ስቴዲየሞች እንደሚካሄድም ጠቁሟል፡፡
ይህን ተከትሎ የመጀመሪያው የሰላም ኮንፍረንስ በድሬዳዋ ከተማ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ታኅሳሥ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
የሰላም ኮንፍረንሱን ዓላማ፣ ሂደትና አተገባበር በሚመለከት የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ነገ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።