ክልላዊ የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር ላይ ያተኮረ መድረክ በቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ክልላዊ የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር ላይ ያተኮረ መድረክ በቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ነው
ሀላባ ፤ታህሳስ 8/2017(ኢዜአ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር አስተባባሪ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ ዛሬ በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመርሐ-ግብሩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የዞንና ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊዎች፤ የፖሊስ አዛዦች እና የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
ርዕሰ መስተዳድሩና ከፍተኛ አመራሩ ቀደም ብሎ በከምባታና ሀላባ ዞኖች የቡና ማሳና ሌሎች ልማቶችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።