የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊዎች የዕውቅና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊዎች የዕውቅና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፤ ታህሳስ 8/2017 (ኢዜአ) :- የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊዎች የዕውቅና መርሃ ግብር በሀዋሳ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ዕውቅናና ሽልማት የሚሰጣቸው በኢትዮጵያ ለአራተኛ ጊዜ በተካሄደው የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር "Cup of Excellence" አሸናፊ የሆኑ 40 አርሶ አደሮች ናቸው።
እነዚህ አርሶ አደሮች በውድድሩ ላይ ቡናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጫርቶም በከፍተኛ ዋጋ ተሽጦላቸዋል።
በዕውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)፣ የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።