ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 8/2017(ኢዜአ):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።
ምክር ቤቱ በስብስባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ይገኛል።
የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርቱን በማቅረብ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።