ቀጥታ፡

የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮ-ታንዛንያ የጋራ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2017(ኢዜአ):- የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና የምስራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በኢትዮ-ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

አምባሳደር ማሕሙድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮ-ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች የመጀመሪያ ስብስባ ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የኮሚሽኑ ስብስባ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት የማጠናከር እና የጋራ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጎልበት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም