ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 7/2017(ኢዜአ):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያደርጋል።

ምክር ቤቱ በስብስባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ይወያያል።

የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል።

ምክር ቤቱም ቋሚ ኮሚቴው የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም