በ195ኛው የማንችስተር ደርቢ ማንችስተር ዩናይትድ ወሳኝ ድል ተቀዳጀ - ኢዜአ አማርኛ
በ195ኛው የማንችስተር ደርቢ ማንችስተር ዩናይትድ ወሳኝ ድል ተቀዳጀ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 6/2017(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ባስቆጠራቸው ግቦች ማንችስተር ሲቲን በሜዳው 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆሽኮ ግቫርዲዮል በ36ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ያስቆጠራት ግብ ሰማያዊዎቹን መሪ አድርጋ ነበር።
ይሁንና ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ88ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና አማድ ዲያሎ በ90ኛው ደቂቃ በጨዋታ ያስቆጠሩት ግብ ማንችስተር ዩናይትድን በደርቢው ጨዋታ ወሳኝ ድል አቀዳጅተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በ22 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 12ኛ ከፍ ማድረግ ሲችል በአንጻሩ ማንችስተር ሲቲ በ27 ነጥብ በነበረበት አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።