ቀጥታ፡

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ነገ በአዳማ ይጀመራል

አዳማ፤  ታህሳስ 6/2017 (ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ነገ በአዳማ የሚጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ነገ በክልሉ የሚጀመረውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ነገ በአዳማ የሚጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ከክልሉ ከ356 ወረዳዎች የተወጣጡ አጀንዳ ሰጪዎች የሚሳተፉበት ነው።

ከ7ሺህ በላይ  የማህበረሰቡ ተወካዮች የሚሳተፉበት ግዙፍ የምክክር መድረክ መሆኑንም አክለዋል።

ኮሚሽኑ ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ስኬት ከክልሉ መንግስት፣ ከአዳማ ከተማ አስተደደር፣ ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲና ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በክልሉ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ከታህሳስ 7 እስከ 15 ቀን 2017ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም