የምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው ኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው ኤሌክትሪክ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6/2017 (ኢዜአ.)፦ የምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አካል የሆነው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኅይል ማስተላለፊያ (ሃይዌይ) ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር ኢትዮጵያና ኬንያን ያስተሳሰረ መሆኑ ይታወቃል።
የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል ደግሞ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋ ሲሆን የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩን ከውሃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ይህ ቀጣናዊ የኃይል ትስስር በተመጣጣኝ ዋጋ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት በማረጋገጥ በሀገራት መካካል ትብብርን እና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የኃይል ትስስሩ ኢትዮጵያን ያላትን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማስፋፋት የአረንጓዴ የኤሌክትሪክ ኃይል ግብይት በቀጣናው እንዲስፋፋ ሚና እንድትጫወት ያስችላል።
በመጀመሪያዎቹ የግብይት ዘመናትም በዓመት ከ200 ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ ገቢ እንደሚያስገኝላት ገልጿል።
ለፕሮጀክቱ የአለም ባንክ ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና የፈረንሳይ የልማት ፋይናንስ ተቋም ድጋፍ አድርገዋል።