የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ
የበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም አርፏል።
ለጥንቃቄ ሲባል መንገደኞች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርጓል።
ሁልጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለክቡራን መንገደኞቹ ደህንነት ቅድሚያ ይሰጣል።
በዚህ አጋጣሚ ውድ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት አየር መንገዱ ይቅርታ እየጠየቀ የቴክኒክ ችግሩ በመጣራት ላይ መሆኑን ይገልፃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ