ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መረቁ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 5/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል።


 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ እየተገነቡ ካሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተጓዳኝ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሸኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ድጋፍ የተገነባውን የኦሮሚያ አብዲ ቦሩ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን መርቀን ከፍተናል ሲሉ ገልጸዋል።


 

ማዕከሉ ወላጅ የሌላቸውንና በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናትን ከማሳደግ ባሻገር የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ትብብር ማሳያ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም