ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በአለታ ጩኮ ወረዳ የተገነቡ የትምህርትና የንጹህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክቶችን መረቁ

ጩኮ፤ ታሕሳስ 4/2017 (ኢዜአ):- የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ አለታ ጩኮ ወረዳ የተገነቡ የትምህርትና የመጠጥ ውሀ ተቋማትን መርቀው ስራ አስጀመሩ።

በምርቃ ሥነ ስርዓቱ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል ሶስት ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሁለት የመጠጥ ውሀ ቦኖዎች ይገኙበታል።


 

በአንድ ባለሀብት የተገነባ 200 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የሚችል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትም ተመርቋል።

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከአለታ ጩኮ ወረዳ በተጨማሪ በዳራ ወረዳ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትንም እንደሚመርቁ ተመላክቷል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም