ቀጥታ፡

የአንካራው ስምምነት ጠንካራ ቀጣናዊ ትብብር መፍጠር የሚያስችል ትክክለኛ እርምጃ ነው -ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 3/2017(ኢዜአ):-በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረሰው የአንካራ ስምምነት በአገራቱ መካከል እና በአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ ቀጣናዊ ትብብር መፍጠር የሚያስችል ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ ገለጹ።

በተርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አቀራራቢነት ትናንት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት በስኬት መጠናቀቁ ይታወቃል።

ፕሬዝዳንት ታዬ፥ ስምምነቱ ከቀጣናው ባሻገር ያለው ፋይዳ ወሳኝ መሆኑን በኤክስ ገጻቸው (በቀድሞው ትዊተር) ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም