ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት የተለያዩ ደረጃዎችን አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት የተለያዩ ደረጃዎችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 3/2017(ኢዜአ)፦ ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት የተለያዩ ደረጃዎችን ዛሬ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ደረጃዎቹን ያጸደቀው በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አማካኝነት የደረጃ አወጣጥና ምደባ አሰራርን ተከትሎ የቀረቡለትን የኢትዮጵያ ደረጃዎች በ40ኛ እና 41ኛ ስብሰባው በጥልቀት ከመረመረ በኋላ ነው።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሰረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንዳለው መኮንን የወጡ ደረጃዎች ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ሁሉም አካላት ደረጃዎቹን እንዲያውቋቸው የማድረግ ስራም በልዩ ትኩረት መስራት እደሚገባ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩትም በምክር ቤቱ አዲስ የጸደቁ ደረጃዎችን ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲያውቋቸው የሚያስችሉ ተከታታይ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ መግለጹን ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።