የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሃረሪ ክልል በልማት ኢኒሼቲቮች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሃረሪ ክልል በልማት ኢኒሼቲቮች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2017(ኢዜአ)፦ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሃረሪ ክልል የልማት ኢኒሼቲቮች የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
ከትናንት ጀምሮ በክልሉ የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ የሚገኙት ሚኒስትሯ በሃረሪ ክልል ከተማና ገጠር የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን፣ በሌማት ትሩፋት በወተት፣ በእንቁላል፣ በማርና በአትክልት ፍራፍሬ ልማት ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እየሆነ ያለበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም በክልሉ በሚገኙ ወረዳዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የግብርና ሥራዎች አርሶ አደሮች ከሴፍቲኔት ተጠቃሚነት እየተላቀቁ መሆናቸውን አርሶ አደሮቹ በምልከታው ወቅት ተናግረዋል፡፡
በተለይም በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በማሽላና ስንዴ ኢኒሼቲቭ የልማት ሥራዎች የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እያደገ መሆኑን መገንዘባቸውን ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በግብርና ኢኒሼቲቭ በተለይም በማሽላ ምርት ላይ እየታየ ያለው ምርታማነት ለሌሎችም አካባቢዎች በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በትምህርት ቤት ግንባታዎችንና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ የልማት ስራዎችንም ተመልክተዋል፡፡
ታሪካዊቷን የሀረር ከተማ ውብ፣ አረንጓዴና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችንና የሃረር ጥንታዊ የቱሪዝም መስህብ የሆነውን የጀጎል ግንብ ዕድሳት ስራም ሚኒስትሯ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡