ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረመ

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 2/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዢያሜን ኤርፖርት ግሩፕ ኩባንያ የስትራቴጂክ ትብብር እንዲሁም ከቻይናው ሄናን አቪዬሽን ግሩፕ ኩባንያ ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።

ስምምነቶቹ ተደጋጋፊ ጠቀሜታዎችን፣የሀብት ተጋሪነት፣የፈጠራ ልማት እና የጋራ ጥቅሞችን መሰረት ያደረጉ መሆኑን አየር መንገዱ ገልጿል።


 

የስትራቴጂክ ትብብር ስምምነቱ የአየር ካርጎ ንግድ ትስስርን ማጠናከር እና በዘርፉ ያለውን የጥራት እድገት መጨመር እንዲሁም ሁለቱ ወገኖች በዓለም የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ያላቸውን የትብብር አድማስ ማስፋት እና ውጤታማ ማድረግን አላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም