የኬንያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
የኬንያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 2/2017(ኢዜአ)፦የኬንያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ አመራሮችና የኮሌጁ ሰልጣኞች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉብኝት አድርጓል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን ለልዑካን ቡድኑ የአየር መንገዱን የተለያዩ አገልግሎቶችና መሠረተ ልማቶችን አስጎብኝተዋል።
ልዑካኑ የአየር መንገዱን የካርጎ ተርሚናል፣ የበረራ መማርያ ሲሙሌተር፣የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ስራንና ሌሎችንም አገልግሎቶች ተመልክተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው የአየር መንገዱን መሠረተ ልማት በማስፋፋትና የዘርፉን ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ በማዋል አገልግሎቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በተሰራው ስራ ውጤታማ መሆን መቻሉን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ለማስተሳሰርና ከዓለም ጋር ለማገናኘት እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በነበራቸው ጉብኝት መደሰታቸውንና ጠቃሚ ተሞክሮ እንዳገኙ መግለጻቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።