ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ በጋራ መቆም ያስፈልጋል - ብርሃነ መስቀል ጠና (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 2/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ በጋራ መቆም እንደሚገባ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርሃነ መስቀል ጠና (ዶ/ር) ገለጹ።

የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርሃነ መስቀል ጠና (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ የሀገሪቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች የኢትዮጵያ የስርዓተ ትምህርት አካል መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ትውልዱ የሀገሩን ወሳኝ አጀንዳዎችና ብሔራዊ ጥቅሞች እንዲያውቅ አበክሮ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ሁሉም አንድ የጋራ ቋንቋ ሊኖረው እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተግባብተው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በተለይም ምሁራን አጀንዳ በመቅረጽ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአፍሪካ ጠንካራ አንድነት የሚበጁ ጥናትና ምርምር፣ የሀሳብ መድረኮችን ሊፈጥሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም