ቀጥታ፡

በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ከታህሳስ 7 እስከ 15/2017 ድረስ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ከታህሳስ 7 እስከ 15/2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍን ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑንና አጀንዳ የማሰባሰብ መርሃ-ግብሩ ከታህሳስ 7 እስከ 15 /2017 ዓ.ም ድረስ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ገልጿል፡፡

በሂደቱም፦ 7 ሺህ 20 የወረዳ የህብረተሰብ ክፍል ወኪሎች፣ 356 ወረዳዎች፣ 1ሺህ 300 የክልል ባለድርሻ አካላት፣ 48 ሞደሬተሮች፣ 356 የክልሉ ተባባሪ አካላት እና 150 በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች እንደሚሳተፉም ኮሚሽኑ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም