የቻይና ኩባንያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያን ቡና የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
የቻይና ኩባንያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያን ቡና የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 30/2017(ኢዜአ)፦የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ቡና በብዛት ለመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ።
የኢትዮጵያ ቡና በቻይናውን ዘንድ ተወዳጅነቱ ይበልጥ እየጨመረ መጥቷል።
ይህን ተከትሎም የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት እና በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ ከቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትስስር መማክርት ልዑካን ጋር ተወያይተዋል።
የመማክርት ልዑካኑ የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቡና ንግድ ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸውና እ.አ.አ በ2025 ከ100 ሺህ እስከ 150 ሺህ ቶን አራተኛ ደረጃ ቡና ለመግዛት ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
መማክርቱ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አመራሮች ቻይና በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያን ቡና በብዛት ከገዙ 10 አገራት አንዷ መሆኗን አመልክተዋል።
በ2017 ዓ.ም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ላኪዎች በድምሩ 100 ሚሊዮን ቶን ቡና ወደ ቻይና ለመላክ እቅድ መያዙን መግለጻቸውን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ቡና በቻይናውያን ተጠቃሚዎች ዘንድ እጅግ እየተወደደ መጥቷል።በተለይም ቻይናውያን ወጣቶች ቡና መጠጣት እያዘወተሩ ይገኛሉ።
ይህን ተከትሎም የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት እና በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።