ቀጥታ፡

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ወረፋን የሚያስቀር የቴክኖሎጂ ሥርዓት ሊተገብር ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 30/2017(ኢዜአ)፦ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ከወረፋ ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚያስቀር የቴክኖሎጂ ሥርዓትን ዛሬ አስጀምራለሁ ብሏል።

ሥርዓቱ የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ በመረጃ ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም ከወረፋ ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚያስቀር የቀጠሮ ማስያዣ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።

አገልግሎቱ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል በቴክኖሎጂ የታገዘ የደህንነት መለያ (Security Feature) ያለው ህትመት እና የኤሌክትሮኒክስ ደረቅ ማህተም መጠቀም መጀመሩን ዛሬ በይፋ ያበስራል።

ተቋሙ መገናኛ እና ቦሌ በሚገኙ ሁለት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ ልዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በተለየ ሁኔታ በማደራጀት ፈጣን አገልግሎት መስጫውን ያስተዋውቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም