ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን ተመለከቱ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 29/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክን መመልከታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።


 

በደቡብ ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከተማ የሚገኘው ብሔራዊ ፓርኩ የሳቫና የሳር ምድርን፣ የደን እና የውቦቹን የአባያ እና ጫሞ ሃይቆች ብሎም የሌሎች ሳቢ መዳረሻዎች መገኛ ሲሆን በተለያዩ መልክዓ ምድሮች ውብ ኅብር የታወቀ የተፈጥሮ መስህብ መሆኑንም ገልጿል።

514 ስኩዌር ኪሎ ሜትሮች የሚሰፋው ፓርክ አይነተ ብዙ ለሆኑ እንደ የሜዳ አህያ፣ አጋዘን፣ አዞ አይነት የዱር እንስሳት ብሎም ከ270 በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች መገኛ በመሆኑ ለተፈጥሮ ጉብኝት አፍቃሪዎች የልብ አድራሽ አይነተኛ ስፍራ ነው ሲልም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።


 

እንደሌሎች ብሔራዊ ፓርኮች ነጭ ሳር የተፈጥሮ ሥነምኅዳርን በመጠበቅ እና ቱሪዝምን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብሏል ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም