ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል - ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ስላሴ - ኢዜአ አማርኛ
ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል - ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ስላሴ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 29/2017(ኢዜአ)፦ ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ስላሴ ገለጹ።
ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ሃሳብ ለ19ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ ሲሉም ፕሬዚደንቱ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀ ስላሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እኛ ኢትዮጵያውያን ሰላምና ነጻነታችን የሚጋፋ ማንኛውንም የውጭ ኃይል በጋራ በማንበርከክ አንድነታቸን ጠብቀን ኖረናል ብለዋል።
ለኅብረ ብሔራዊ ሀገሩ ቀናዒ የሆነ፣ ልማትን ዕውን ለማድረግ የወሰነ ትውልድ፣ ሰላሙንም በአስተማማኝነት ያፀናል ሲሉም አክለዋል።
ካለመግባባት የምናተርፈው፣ ከልማት የምናጣው፣ ከሰላም የምናጎድለው እንደሌለ ከእኛ የተሻለ የተገነዘበ ሊኖር አይችልም ብለዋል።
ስለሆነም፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በዕኩልነትና በፍትህ መሠረቶች ላይ ይበልጥ በማፅናት ጠንካራ፣ የበለፀገች፣ የታፈረችና የተከበረች ኢትዮጵያን እንገንባ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።