በደቡብ ዕዝ የ202ኛ ተወርዋሪ ኮከብ ኮር 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዳማ እየተከበረ ይገኛል - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ዕዝ የ202ኛ ተወርዋሪ ኮከብ ኮር 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዳማ እየተከበረ ይገኛል

አዳማ፤ ህዳር 29/2017(ኢዜአ)፦ በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ የ202ኛ ተወርዋሪ ኮከብ ኮር 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በአዳማ እየተከበረ ይገኛል።
የዕዙ 3ኛ ዓመት የምስረታ በዓል "ተወርዋሪ ድል አብሳሪ" በሚል መሪ ሐሳብ በአዳማ ከተማ እየተከበረ ነው።
በክብረ በዓሉ ላይም "በምንከፍለው መስዋዕትነት ሀገራችን ኢትዮጵያ ፀንታ ትኖራለች"፣ "ህብረብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ በማጠናከር የሀገራችንና ተልዕኳችንን በብቃት እንወጣለን የሚሉ መልዕክቶች በመሰማት ላይ ናቸው።
በሁነቱ በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ እና የሜካናይዝድ ዕዝ አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴን ጨምሮ የተለያዩ ወታደራዊ አመራር አባላት፣ የአዳማ ከተማ፣ የምስራቅ ሸዋ፣ የአርሲ፣ የምዕራብ አርሲ፣ የባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች አስተዳደሮች አመራር አባላትና የየዞኖቹ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።