የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በአፋር ክልል የወባ በሽታን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እየተመለከቱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በአፋር ክልል የወባ በሽታን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እየተመለከቱ ነው

ሠመራ፤ህዳር 29/2017(ኢዜአ)፦የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በአፋር ክልል ሠመራ ሎጊያ ከተማ የወባ በሽታን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እየተመለከቱ ነው።
ሚኒስትር ዴኤታው በክልሉ ሠመራ ሎጊያ ከተማ ለወባ በሽታ መከላከል እየተደረገ ያለውን ሥራ በተመለከተ ያለውን እንቅሰቃሴ ለመደገፍ ሎጊያ ጤና ጣቢያ ተገኝተዋል።
በምልከታቸውም የወባ በሽታን ለመከላከል በተደረገው ዘመቻ የመራቢያ ቦታዎችን ማጥፋትና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ላይ የተከናወኑት ተግባራትን ተመልክተዋል።