ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ወደ ነበረበት እየተመለሰ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል - ኢዜአ አማርኛ
ተቋርጦ የቆየው የኃይል አቅርቦት ወደ ነበረበት እየተመለሰ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦ ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል አቅርቦት ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።
በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩንም ተቋሙ ገልጿል።
የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል አቅርቦት ደረጃ በደረጃ መመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው ተቋሙ ጨምሮ ያስታወቀው።
ደንበኞችም የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጠይቋል።