የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦ በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት በተፈጠረ ችግር በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ እንዳጋጠመ ገልጿል፡፡

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስም በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ እና ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት እንደሚያሳውቅም አገልግሎቱ በመረጃው አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም