ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በ19ኛው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም አርባ ምንጭ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በ19ኛው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም አርባ ምንጭ ገብተዋል።

አርባምንጭ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ኃሳብ በነገው ዕለት ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም