ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የ2017 ዓመታዊ የክለቦች ውድድር ምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የ2017 ዓመታዊ የክለቦች ውድድር ዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተከናውኗል።

ለ9ኛ ጊዜ በሚከናወነው ዓመታዊ ውድድር 10 ክለቦች የሚሳተፉ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ለመገናኛ ብዙሃን በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። 

የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞላ ተፈራ፤ ውድድሩ በሐዋሳ፣በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል።

ውድድሩ በሁለት ዙር ተከፍሎ እንደሚደረግና የመጀመሪያው ዙር በሐዋሳና በአዲስ አበባ ከተማ፤ ሁለተኛው ዙር ደግሞ በድሬዳዋና በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከናወን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አስታውቀዋል።

ውድድሩ ከታኅሳስ 6 እስከ ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚደረግም ተናግረዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም