የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦ የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ ለስራ ጉብኝት ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባሉ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክን የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ኢዜአ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጁሬስካ ከውይይታቸው በተጨማሪ የአድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶችና ቦታዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ በጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዳር ወር 2016 ዓ.ም በቼክ ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውም አይዘነጋም።
የኢትዮጵያና የቼክ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደ አውሮፓውያን አቆጠጣር በ1993 እንደተጀመረ መረጃዎች ያሳያሉ።
ሁለቱ ሀገራት በግብርናና ገጠር ልማት፣ በሕዝብ አስተዳደርና ሲቪል ማኅበረሰብ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ ማኅበራዊ ልማት ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር እየሰሩ ይገኛሉ።