ቀጥታ፡

የ5 ኪሎ ሜትር ሲቢኢ ሩጫ ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ የሚያደርገው ወርሃዊ የሩጫ ውድድር ዛሬ ተካሂዷል።

በሩጫ ውድድሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ውድድሩ የህብረተሰቡን ጤናማ አኗኗር ባህል ለማድረግ በየወሩ የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል።

5 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም