ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 450 የአቪዬሽን ባለሙያዎች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የአውሮፕላን አብራሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ የአቪዬሽን የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 450 ሙያተኞች እያስመረቀ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የፋይናስ ዘርፍ ኃላፊ አዳሙ ታደለ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።


 

ስልጠናውን ተከታትለው ያጠናቀቁ የዘርፉ ሙያተኞች ቁጥርም 450 መሆናቸው ታውቋል።

በዚህም 115 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ 123 የበረራ መስተንግዶ ባለሙያዎች፤ 84 የጥገና ዘርፍ እና 128 የኮሜርሻል ዘርፍ ሙያተኞች ስልጠናውን መከታተላቸው ተገልጿል።

ሰልጣኞቹም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትና ከሌሎች የተለያዩ አህጉራት የተውጣጡ መሆናቸውም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም