የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በአርባ ምንጭ ከተማ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በአርባ ምንጭ ከተማ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው
አርባ ምንጭ፤ህዳር 28/2017 (ኢዜአ)፡-19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲምፖዚየም በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሎች ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተዋል።
የብሔረሰቦች ተወካዮች፣ አባገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎችም እንዲሁ።
በሲምፖዚየሙ ላይ ሀገረ- መንግስት ግንባታ በህብረ-ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት እና የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ ነገ በአርባ ምንጭ ከተማ ይከበራል።