ቀጥታ፡

ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በዓሉን ለመታደም አርባ ምንጭ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው

አርባ ምንጭ፤ህዳር 27/2017 (ኢዜአ)፡-በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መጥተው አርባምንጭ ከተማ የገቡ እንግዶች አቀባበል እየደረገላቸው ይገኛል።

እንግዶቹ አርባምንጭ ከተማ ሲደርሱ አቀባበል እያደረጉላቸው ያሉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ አመራር አባላትና ነዋሪዎች ናቸው።

እስከሁን አቀባበል ከተደረገላቸው መካከል ከትግራይ ክልል የመጡ የባህል ቡድን አባላት ይገኙበታል።

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የባህል ቡድኖች አባላት ተጠቃለው አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንደሚተላለፍ ይጠበቃል።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ህዳር 29/2017ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም