ቀጥታ፡

አየር መንገዱ ለናይጄሪያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፤ህዳር 27/2017(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለናይጄሪያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዕድገት እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ ሽልማት ተበርክቶለታል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያገኘው በናይጄሪያ አቡጃ በተካሄደው የቱሪዝምና ትራንስፖርት ኤክስፖ ላይ ነው።

በዚህም ለናይጄሪያ የቱሪዝም ኢንደስትሪ ዕድገት በዓየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ "Outstanding Onboarding Experience Achievements” ሽልማት አግኝቷል።

ይህ ዓመታዊ የቱሪዝም ኤክስፖ የትራንስፖርት ትስስር ለቱሪዝም ዕድገት በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በአፍሪካ ቱሪዝም ዘርፍ ላይ ወሳኝ ሚና ያላቸው የተለያዩ ተቋማት እንደሚሳተፉበት ከአየር መንገዱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም